የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት እና የአደጋ ስጋት መኖሩን ከተረዳን እንደ ተቋም ሊወሰዱ የሚገቡ ቀዳሚ እርምጃዎች ምንድን ናቸው?
የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት እና የአደጋ ስጋት መኖሩን ከተረዳን እንደ ተቋም ሊወሰዱ የሚገቡ ቀዳሚ እርምጃዎች ምንድን ናቸው? የሳይበር ምህዳሩ የሰዉ ልጆችን የእለት ተእለት የኑሮ ዘይቤ ቢያዘምነዉም በዚያዉ ልክ ተጋላጭ በማድረጉ ሚስጥራዊ ብለን ያስቀመጥናቸዉ ግለሰባዊ፣ ተቋማዊ እንዲሁም ሀገራዊ መረጃዎችን በቅጽበት ሲያሳጡን መስማት እና ማየት የተለመደ ሆኗል። ብዙዉን ጊዜም የሳይበር ጥቃቶች ከአጠቃቀም ግድፍት ወይም ሆን ተብሎ በመረጃ መንታፊዎች በሚፈጸም ጥቃቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። በመሆኑም ተቋማት የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት መኖሩን ካወቁ ምን እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል የሚለዉን ከዚህ በታች ተዘርዝረዉ እናገኛቸዋለን። • የተቋሙን መረጃዎች መጠበቅ:- በሳይበር ጥቃት ተጠቅተው ሊሆኑ ይችላሉ ብለው የሚያምኗቸውን ፋይሎች ከሌሎች መረጃዎ ለይቶ ማስቀመጥ፤ • ሰርቨሮችን መቆጣጠር:- የትኞቹ ሰርቨሮች ጥቃቱ እንደተሰነዘረባቸው መለየት እና ጥቃቱ እንዳይሰራጭ ከሌሎች ሰርቨሮች እና መሳሪያዎች መለየት እና የደህንነት መቆጣጠሪያ መተግበሪያዎችን መጫን፤ • ተጨማሪ_ጉዳቶች እንዳይደርሱ እርምጃዎችን መዉሰድ:- ከተቋሙ ሰርቨሮች ጋር የተያያዙ ባለድርሻ አካላት ካሉ ስለተከሰተዉ ጉዳይ ማሳወቅና ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረጋቸውን ማረጋገጥ፤ • የተቋሙን_የኢንፎርሜሽን_ቴክኖሎጂ (IT) ስርዓቶችንና ሲስተሞች እንዲሁም የተቋሙን ፖሊሲዎች እና ስታንዳርዶች ተጣጣሚነታቸውን፣ ያሉትን ክፍተቶች መገምገም መከለስና እርምጃ መዉሰድ፤ • የኢ_ሜይል አቅራቢዎች እና ፀረ- ቫይረስ ፕሮግራሞችን መፈተሽ፡- የጥቃቱን ወቅታዊ ሁኔታ፣ የጥቃቱ መንገዶች እንዲሁም ለጥቃቱ ሰለባና እንደ መግቢያ በር ሆነው ሙሉ ስርዓቱን እንዲጠቃ የሚያደርጉትን የሲስተሙ ክፍሎች መለየ...