Posts

Showing posts from March, 2025

ክሎኒንግ አለያም ስዋፒንግ ምንድን ነው?

  ክሎኒንግ አለያም ስዋፒንግ ምንድን ነው? የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በርካታ አዳዲስ ነገሮችን አስተዋውቆናል። ከእነዚህ መካከል አንዱ ክሎኒንግ ነው።  ክሎኒንግ የሚለው ቃልም የተለመደ እየኾነ መጥቷል። የቃሉ ጥሬ ትርጓሜ ለአንድ ነገር ተመሳሳይ ቅጂ የመፍጠር ሂደት ነው፡ ፡  ቃሉ ከቴክኖሎጂ ባሻገር በሥነ ሕይወትም የህዋስን ጄኔቲካዊ ቅጂ ከመፍጠር ጋር ተያይዞ ሲገለጽ እንሰማለን።   ዲጂታል ክሎኒንግ ደግሞ ለምሥሎች፣ ድምጾች እና ቪዲዮዎች ተመሳሳይ ቅጃቸውን መፍጠር ነው። ክሎኒንግ በዲጂታል ዓለም የሰዎችን ማንነት በአዲስ መልክ በመግለጽ፣ የመዝናኛውን ኢንዱስትሪ በማዘመን፣ በሥራ መሥክ ስጋቶችን እና በረከቶችን በመፍጠር፣ ባሕላዊ እና ማኅበራዊ ኹኔታዎችን በማቀራረብ እና ታሪክን በመሰነድ አገልግሎት ላይ ይውላል። ክሎኒንግ በዲፕፊክ ውስጥ ያለ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የፈጠረው የቴክኖሎጂ ውጤት ሲኾን የምስል ቅጂን የመፍጠር ሂደትን ስዋፒንግ እንለዋለን። ለድምጽ ከኾነ ደግሞ የድምጽ ክሎኒንግ ይባላል።  ብዙ ጊዜ የምስል ቅጂን ለመዝናኛ፣ የሰዎችን ምሥል ላልተፈላገ ዓላማ ለመጠቀም እና የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመልቀቅ ይጠቀሙበታል።  የድምጽ ክሎኒንግ የአንድን ሰው ድምጽ አስመስሎ የእውነትም ይኹን የሐሰት መረጃዎችን ለማጋራት፣ ለመዝናኛ አገልግሎት እና ያለፈን ታሪክ በአዲስ ምናባዊ አቀራረብ ለማቅረብ ሲባል አገልግሎት ላይ ሊውል ይችላል።     ይህን ቴክኖሎጂ ወደ ተሻለ ደረጃ በማሳደግ ረገድ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የላቀ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።  ቴክኖሎጅው ከማደጉ ጋር ተያይዞ በክሎኒንግ የሚፈጠሩ የሐሰት መረጃዎች ሰዎች ለመለየት እስከሚያዳግታ...

የሰዎችን ስነልቦናና ባህሪይን በማጥናትና በመቆጣጠር ስለሚፈጸመዉ የሳይበር ጥቃት ምን ያክል ያዉቃሉ?

Image
  የሰዎችን ስነልቦናና ባህሪይን በማጥናትና በመቆጣጠር ስለሚፈጸመዉ የሳይበር ጥቃት ምን ያክል ያዉቃሉ? የሰዎችን ስነ-ልቦናና ባህሪይን በማወቅና በመቆጣጠር የሚፈጸም የሳይበር ጥቃት አይነት ማህበራዊ ምህንድስና #social_engineering ጥቃት በመባል ይታወቃል። በጥቃቱ የግለሰብ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ወይም ሲስተሞችን ለመቆጣጠርና ጉዳት ለማድረስ የሰውን ልጆችን ስህተትና ድክመት እንደ መልካም እድል ይጠቀማል።  ይህ ጥቃት አይነትለወራት ወይም ለቀናት በኢ-ሜይል መልዕክት ወይም በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያና የተግባቦት መንገዶች በሚደረግ ክትትልና ግንኙነት ላይ በመመስረትና የተጠቂዉን ደካማጎን በመለየት ይፈጸማል።  የሰዎችን ስነልቦናና ባህሪይን በማጥናትና በመቆጣጠር የሚፈጸም ጥቃት #social_engineering ለማድረስ የሚከተሉት ደረጃዎች ይታለፋሉ፦  👉1. የጥቃት ኢላማ ስለተደረገዉ አካል መረጃ የመሰብሰብ ደረጃ፤   👉2. ግንኙነት በመመሥረት ወይም መስተጋብርን በመፍጠር እምነት የመገንባት ደረጃ 👉3. በድክመቶቹ ላይ ተመስርቶ ጥቃት መሰንዘሪያ ደረጃ 👉4. መረጃ ከወሰዱና አጥፊ ሶፍትዌር ካሰራጩ በኋላ ግንኙነቱን የማቋራጥ ደረጃ

አንድ የበቾ ገበሬ... የኛ ሃገር መሬት በትራክተር ሢታረሥ ምርቱን ይቀንሥብኛል የሚል ሃሣብ አወጋኝ።

Image
 አንድ የበቾ ገበሬ... የኛ ሃገር መሬት በትራክተር ሢታረሥ ምርቱን ይቀንሥብኛል የሚል ሃሣብ አወጋኝ። ~~~~~~ የ ደጀኔ አያት ጺምና ሚሥጥሩ! [ቀመቀምኩኝ እንጂ አላጨውትም።😍] የደጀኔ አያት ጺሙን  ሁሌ በመቀሥ ይከመክማታል እንጂ ዝቅ ብሎ አይቆርጣትም። "እንደ ድንች፣እንደ ጥበብ- ጥበቡ ያለው ከሥር ነው " ይላል በመሥታወት ውሥጥ አሻግሮ የጎሪጥ ደጀኔን እየተመለከተ። ¤ [በሬ ሆይ ሣሩን አይተህ ገደሉን ሣታይ...] ደጀኔ የውርሥ እንጂ የእቅድ ገበሬ አይደለም። ይህንን ሃሣብ ግን  ሁሌ ይከታተል ነበር። እንደ አያቱ ጺም....  'እርሻዬ ከታች የተደበቀ ነገር ካለ በሚል እሣቤ ፣ የኔም እርሻ- አፈሩ ፣ማሣው ሚሥጥር  ውሥጡ ይኖረዋል'   በሚል አሥተውሎ....  የበሬዎቹ ጫንቃ  እሥኪላጥ ፣ጅራፉ እሥኪበጣጠሥ፣ድምጹ እሥኪዘጋ፣እርፉ እሥኪሠበር ፣ሚሥቱ እሥክትደክም... እንዳበደ ገበሬ   ማሣውን ቆፈረው፣ ጎደፈረው፣ አረሠው።  በአዲሥ ማረሻው፣ ከ30cm በታች  ሙሉውን መሬት ገለበጠው-(SPF) sun protection factor  አልገባውማ። ¤ ዘራበት!ተከለበት! እነ በቆሎ፣እነ ካሮት፣እነ ድንች ፣እነ ሥንዴ፣እነ ባቄላ፣እነ አኩሪ አተር፣እነ ሸንኮራ  ተደሠቱ - አቆጠቆጡ። ሥሮቻቸው ድግሥ ወጡ፣ ቅጠሎቻቸው  ተቻረሡ፣ግንዶቻቸው አሸበረቁ።ደሥ አላቸው።ቁመታቸው እኩል ነበር። 'ሥራችን ሠደደ፣አየራችን ተሥማማ፣ምግባችን በዛልን' አሉ።ተመቻቸው። ¤ [አሉም....] 'እኔ በቆሎ ሣድግ፣ሥመነደግ ብዙ ፍሬ ለጌታዬ አሥገኛለሁ። እንደ ድንች እራሤን ቀብሬ ብርሃን እጦት አያጠቃኝም ' አለ። 'እኔ ድንችሥ የአፈሩን አየር፣የምድሩን በረከት በገላዬ ሁሉ ...

በስፋት እየተከሰቱ ያሉ ማጭበርበሮች በምን መልኩ ሊፈጸሙ ይችላሉ?

Image
 በስፋት እየተከሰቱ ያሉ ማጭበርበሮች በምን መልኩ ሊፈጸሙ ይችላሉ? ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሃገራችንም የሚከሰቱ የማጭበርበር ወንጀሎች ቁጥራቸዉ ክፍ እያለ መጥቷል። ከማጭበርበር ጋር በተያያዘም ለሚመለከታቸዉ የህግ አስከባሪ አካላት በተደጋጋሚ ሪፖርቶች ይቀርባሉ። በመሆኑም ግለሰቦች የሚፈጸሙ ማጭበርበሮችን ለመከላከል በቅድሚያ በምን መልኩ ሊጭበረበሩ እንደሚችሉ ማወቅ ይገባል። በዚህ ጽሁፍም አጭበርባሪዎች በምን መልኩ ወደእኛ ቀርበዉ ሊያታልሉን የሚችሉበትን መንገድ እንጠቁማችሁ፡ 👉#በፍቅር_ጓደኝነት_ስም አጭበርባሪዎች የፍቅር ግንኙነትን ወይም ጓደኝነትን እንደ ወጥመድ ይጠቀማሉ። እነዚህ ግንኙነቱ እውነት እንዲመስል ጠንክረው የሚሰሩ ሲሆን የወጥመዳቸዉ ሰለባ የሆኑ አካላትን ከፍተኛ ገንዘብ ያጭበረብራሉ።   👉#ትርፍ_ለማግኘት_ባለን_ፍላጎት  ትርፍ ለማግኘት በምናደርጋቸዉ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ አጭበርባሪዎች እኛን ለማማለል በቀላሉ ብዙ ገንዘብ የምናገኝበት አማራጭ እንዳላቸዉ በማስመሰል ሁሉንም አይነት የማጭበርበር ዘዴ በመጠቀም ገንዘባችንን ይወስዳሉ።  👉#የምርት_እና_አገልግሎት_አቅራቢ_በመምሰል አጭበርባሪዎች ምርቶችን እና አገልግሎቶችን የሚገዙ ወይም የሚሸጡ በመምሰል ሰዎችን በማጥመድ ያጭበረብራሉ።  👉#በማስፈራራትና_በዛቻ አጭበርባሪዎች የእኛን ማንነት ወይም ገንዘብ ለማጭበርበር ማንኛውንም ታክቲክ የሚጠቀሙ ሲሆን ግላዊ መረጃዎቻችንን መጥለፍና ከመለጠፍ እስከ የግድያ ዛቻ በማስፈራራት ሊያጭበረብሩን ይችላሉ።  👉#በስራ_ቅጥር_ስም  ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኝ ሥራ እንደሚያስቀጥሩን በማግባባት ለቅጥሩ ቅድመ ክፍያ በመጠየቅ ገንዘባችንን አሳልፈን እንድንሰጣቸው በማድረግ ሊያጭበ...

ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን ለመለየት የሚያስችሉ ምልክቶች || How to Identify Fake Social Media Accounts‼️

Image
ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን ለመለየት የሚያስችሉ ምልክቶች በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ከ4-6 በመቶ የሚሆኑት አካውንቶች ሀሰተኛ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ። በተለይ የቴክኖሎጂ እውቀት ለሌላቸው ሰዎች ሀሰተኛ አካውንቶችን ለመለየት ከባድ ሊሆን ይችላል።  አንድን የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት ሀሰተኛ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ለመለየት ፍንጭ የሚሰጡ አንዳንድ ምልክቶች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል።  1. ስለአካዉንቱ ባለቤት ዝርዝር መረጃ አለመያዝ፤ 2. ከጉግል ወይም ከሌሎች ድረ-ገጾች የተገኙ ፎቶዎችን መጠቀም፤ 3. በብዛት ሌሎችን መከተል (follow) ማድረግና በአንጻሩ ጥቂት ሰዉ ይከተላቸዋል፤ 4. ወጥነት የሌለው እንቅስቃሴ ማሳየት፤ 5.  በአብዛኛው አወዛጋቢ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች መለጠፍ፤ 6.  የወል ርእስ ወይም ኦሪጅናል ያልሆነ ይዘትን መጠቀም፤  7.  ግብስብስ መልዕክቶችን፣ አጠራጣሪ ሊንኮችንና ወጥ ያልሆነ ሃሽታጎችን ያጋራሉ፤  8.  ለአንድ ርዕስ በጣም አወንታዊ ወይም አሉታዊ ይሆናሉ (ዋልታ-ረገጥነት)፤

የልጆቻችን እጣፈንታ እና ChatGPT

Image
የልጆቻችን እጣፈንታ እና ChatGPT ChatGPT የተሰኘው AI በOpenAI ካምፓኒ የሚሰራ ሲሆን አሁን ላይ አስደንጋጭ በሚባል ደረጃ እያደገና እየዘመነ መጥቷል:: ከፎቶ ጀምሮ realistic Videoን እና በተጨማሪም ድምፅን አስመስሎ ጀነሬት በማድረግ የግለሰቦችን ሕይወት እያመሰቃቀለ ይገኛል። "የኛውስ የኛው ነው ይበለን" ነገር ግን ዛሬ ላይ ነፍስ ያላወቁ የልጆቻችን ፎቶ በማህበራዊ ገጾች ላይ እንደቀልድ እየለጠፍን Dataቸውን(የህፃናቱን ገጽታ፣ የልደታቸውን ቀን እና የመሳሰሉትን) ለ ChatGPT ያለፍቃዳቸው ተጋላጭ እያደረግናቸው እንደሆነ እና ነገ ላይም የህፃናቱን ስነልቦና ሊጎዳ የሚችል አዲዮ-ቪድዮ በልጆች ገጽታ እና ስነባህሪ ፍፁም ተመሳሳይ የሆነ ጀነሬት ሊያደርግ እንደሚችል በአጽንኦት ልንገነዘብ ይገባል። እንደምሳሌ የቴዲ ዬ "ይለያል ዘንድሮ" የሚለውን የሙዚቃ ቪድዮ ማቅረብ ይቻላል። የኋላ ኋላም AI(Artificial Intelligence) የልጆች ስነልቦና ላይ ጫና በማሳደር የልጆቻችን የቤተሰብ ምርጫ ከሰው ዘር ወደ ሮቦት ማለትም "አባቴ፤ የሚሞተው ሰው የሆነው" ሳይሆን "የኔ አባት Eternal(ዘላለማዊ) የማይሞተው ዲጅታል ቅጅ(Cloned) የሆነው ሮቦት ነው" ሊሉ እንደሚችልም መጠርጠሩ አይከፋምና ቶሎ ሳይቃጠል በቅጠል ማለቱ ተገቢ ነው

አስተማማኝ የይለፍ ቃሎችን በምን መልኩ እንፈጥራለን? How to create strong Password?

Image
 አስተማማኝ የይለፍ ቃሎችን በምን መልኩ እንፈጥራለን?  በመረጃ መንታፊዎች ወሳኝ መረጃዎቻችንን እንዳይወሰድብንና አካዉንቶቻችን ከኛ ቁጥጥር ዉጪ እንዳይሆኑ ለምንጠቀማቸዉ ማንኛዉም አካዉንቶቻችን ጠንካራና በቀላሉ ልናስታዉሰዉ የምንችለዉን የይለፍ ቃል መፍጠር ጠቃሚ ነዉ። በመሆኑም የይለፍ-ቃል ስንፈጥር የሚከተሉትን አማራጮች መጠቀም ይመከራል፡-   👉ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (2FA) መጠቀም፤ 👉የይለፍ ቃሎችንን የቁጥሮች፣ ምልክቶች እና የሆሄያት ስብጥር መፍጠር፤ 👉የይለፍ-ቃልዎን ቢያንስ ስምንት የሚሆን የፊደላት፣ቁጥሮችና ምልክቶችን እንዲይዝ ማድረግ: 👉ለይለፍ-ቃልዎን በማይረሱ ምህጻረ ቃሎችንና አባባል መጠቀም፤ 👉የይለፍ-ቃልዎን በመደበኛነት መለዋወጥ፤

አዲሱ ቻት ጂፒቲ!

Image
አዲሱ ቻት ጂፒቲ! ኦፕን ኤ.አይ እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም በዓለማችን ትልቅ ሥም ባላቸው ሥራ ፈጣሪዎች እና የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ ላይ ምርምር በሚያደርጉ ግለሰቦች የተመሠረተ ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው ከምስረታው ጀምሮ አምስት ጊዜ ማሻሻያ የተደረገበትን ቻት ጂፒቲ የተሰኘ ቻት ቦት ለዓለም በማበርከት ለተለያዩ ተግባራት ማሳለጫ ኾኖ እያገለገለ ያለን የሰው ሠራሽ አስተውሎት አበርክቷል፡፡ ቻት ጂፒቲ በጽሑፍ በሚደረግ ተግባቦት ከኮምቲውተሮቻችን ጋር በማውራት የተለያዩ ሥራዎችን እንድናከናውን ይረዳናል፡፡ በዋናነት የይዘት ሀሳቦችን በማመንጨት፣ ሒሳብን በማስላት እና የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን በመቀመር የሰዎችን ሕይወት የሚያቀል እገዛን ያደርጋል፡፡ ቻት ጂፒቲ እስከ አኹን በተደረገለት የዝማኔ ማሻሻያ ጂፒቲ 3፣ ጂፒቲ 3 ነጥብ 5፣ ጂፒቲ 4 እና ጂፒቲ ቱርቦ የሚባሉ ሂደቶችን አልፏል፡፡ ከቀናት በፊት ይፋ የተደረገው ደግሞ ጂፒቲ 4 ነጥብ 5 ይሰኛል፡፡ አኹን የደረሰበት ለውጥ እጅግ የላቀ የሚባል ማሻሻያዎችንም ያካተተ ነው፡፡ አዲሱ ቻት ጂፒቲ የላቀ የስሜት ብልህነትን (Enhanced Emotional Intelligence) የተላበሰ በመኾኑ ከሰዎች ጋር ተፈጥሯዊ ሊባል በሚችል መንገድ ተግባቦት ማድረግ ይችላል፤ አኹናዊ የድረ ገጽ መረጃዎችን ማግኘት የሚያስችል ሥርዓት ስላለውም ተለዋዋጭ ኹኔታዎችን መረዳት ይችላል፡፡ የፈጠራ ሀሳብን የማመንጭት አቅሙ ስላደገ ጥሩ የጽሑፍ ይዘቶችን ማዘጋጀት ይችላል፤ በመማር ሂደቱ (Learning Process) ብዙ የቋንቋ እና የባሕል አውድን የሚረዳ በመኾኑ የተሻለ አውድ የመረዳት ብቃት አለው፡፡ በተጨማሪም በሰው ሠራሽ አስተውሎት ላይ በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈጠሩ ከእውነታ እና ዐውድ የራቁ የመረጃ ቅንብሮች ...

የሳይበር ሉዓላዊነት

የሳይበር ሉዓላዊነት የሀገር ሉዓላዊነት ሲነሳ መልከዓ ምድራዊ ሉዓላዊነት ብቻ ይምሰል እንጅ ዘርፈ ብዙ እንደኾ በኢንፎርሜሽን ደኅንነት አገልግሎት የኢንፎርሜሽን ኢንሹራንስ ዘርፍ አሥተባባሪ የኾኑት ሃኒቫል ለማ ይገልጻሉ፡፡ የሳይበሩ ዓለም ቀደም ተብሎ የሚታሰበውን የሉዓላዊነት ኹኔታ እንደቀየረው አሥተባባሪው ይናገራሉ፡፡ ይህም የቃሉን መገለጫ ስለመቀየሩ ነው የነገሩን፡፡ ከዚህ በፊት በምናውቀው የሉዓላዊነት ጽንሰ ሃሳብ መልከዓ ምድራዊ ድንበርን ብቻ ነበር የምናውቀው የሳይበሩ ዓለም ላይ ግን የሉዓላዊነት ጉዳይ ድንበር የለሽ ነው ይላሉ፡፡ የሳይበር ሉዓላዊነት እስከ ግለሰብ ድረስ የሚወርድ በመኾኑ የግለሰቦችም የሳይቨር ደኅንነት መጠበቅ እንደሚኖርበት ነግረውናል፡፡ የአንድ ግለሰብ የሳይበር ምህዳር መጠበቅ በዙሪያው ያሉትን ቤተሰቦቹን፣ ማኅበረሰቡን ክፍ ሲልም ከሀገር ጥቅም ጋር የሚያያዝ እንደኾነም ነው የተናገሩት፡፡ በግለሰብ ደረጃ ያለን የሳይበሩ ሉዓላዊነት መጠበቅ ሀገርን መጠበቅ እንደኾነ ነው ያስገነዘቡት፡፡ በሀገር ደረጃ የሳይበር ሉዓላዊነትን መጠበቅ ሲባል የምንጠቀምባቸው ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን መጠበቅ ይኾናል ነው ያሉት፡፡ እነዚህን መሠረተ ልማቶችን መጠበቅ ደግሞ ከግለሰብ እስከ ሀገር ድረስ የሚደርስ ጥቅም እንደሚኖረው ያስረዳሉ፡፡ ይህም ከሀገራዊ ሉዓላዊነት ጋር እንደሚገናኝ ነው ያብራሩት፡፡ የሳይበር ጥቃት ሲባል በየቀኑ በተሳሳቱ መረጃዎች እና መረጃ በማዛባት በግብይት ወቅት የሚጠቃውን ሰው ጨምሮ በሀገር ደረጃም አስፈላጊ መሠረተ ልማቶችን እንዳይሠሩ ማድረግን፣ የፋይናንስ አገልግሎቶች በአግባቡ እንዳይሠሩ ማድረግ፣ መንግሥት ለዜጎች ሊሰጠው የሚገባውን አገልግሎት እንዳያደርስ ማስተጓጎል እንደሚገኙበት ተናግረዋል፡፡ በሰፊው ስንመለከተው እነዚህን መጠበቅ አስፈላጊ ...

በመድኃኒት እና በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ላይ ተአምር ይፈጥራል የተባለው የጉግል ፈጠራ

Image
  በመድኃኒት እና በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ላይ ተአምር ይፈጥራል የተባለው የጉግል ፈጠራ ************************************************* አሁን ላይ ካሉ ኮምፒውተሮች እጅግ ፈጣኑ የሚባለው ኮምፒውተር አንድን ችግር ለመፍታት ወይም የሒሳብ ስሌትን ለማጠናቀቅ አሥር ስፒትልዮን ዓመት የሚወስድበት ቢሆን፣ ይህንኑ ስሌት በአምስት ደቂቃ ውስጥ የሚሠራ አዲስ ቺፕ መፍጠር መቻሉን ጉግል ገልጿል። አሥር ስፒትልዮን ዓመት በቁጥር ሲጻፍ ከአስር በኋላ ሃያ አራት ዜሮዎችን የሚያስከትል ቁጥር ነው። ይህም ማለት 10,000,000,000,000,000,000,000,000 ይሆናል። አንድን ስሌት ለማጠናቀቅ ፈጣል የሚባለው ኮምፒውተር ይሄን ሁሉ ዓመታት ቢወስድበትም የጉግል አዲስ ፈጠራ ግን ስሌቱን በአምስት ደቂቃ ውስጥ እንደሚጨርሰው ተነግሯል። ጉግል የሠራው ቺፕ በኳንተም ኮምፒውቲንግ ዘርፍ አዲስ ፈጠራ ነው። ለዚህ ቺፕ 'ዊሎው' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። እጅግ አስደናቂ ፍጥነት ያለው እና አስገራሚ የሆነ ቺፕ ነው። "በላቀ ደረጃ ለሚሠራ ኳንተም ኮምፒውተር መንገድ የሚከፍት አስደናቂ ፈጠራ" በሚል ነው የተገለጸው። ይህ ፈጠራ አሁን ገና በሙከራ ደረጃ ነው የሚገኘው። ውስብስብ ስሌቶችን መሥራት የሚችል ኳንተም ኮምፒውተር ለመሥራት አሁን ዓመታት ይቀራሉ። በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚጠይቅም ሥራ ነው። ኳንተም ኮምፒውተር ******************** ኳንተም ኮምፒውተር ከስልክ ወይም ከላፕቶፕ በተለየ መንገድ ነው የሚሠራው። ኳንተም ማለት ከማንኛውም ቁስ አካል አንሶ የሚገኝ ወይም ቅንጣት ሊባል የሚችል ነው። ኳንተም ሜካኒክስን በመጠቀም አሁን ጥቅም ላይ እየዋሉ ካሉ ኮምፒውተሮች እጅግ በፈጠነ ሁኔታ ማንኛውንም ነገር ማከናወን ላይ ምር...

ኮምፒውተርን ፈጣን ለማድረግ || To make your computer faster !!

Image
  ኮምፒውተርን ፈጣን ለማድረግ፡- ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡ አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡ የማይጠቀሙበት ሶፍትዌር ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት)፡፡ ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡ ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፕ አይነት አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ፡፡ Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ:: ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡ ኮምፒውተርዎን update ያድርጉ!

የግል መረጃዎችን በኢንተርኔት ብናጋራ ምን ይገጥመናል?

Image
የግል መረጃዎችን በኢንተርኔት ብናጋራ ምን ይገጥመናል? የግል መረጃዎቻችን እኛን ከሌሎች ለመለየት የሚያገለግል ማንኛውም ዳታ ነው። ከግል መረጃዎቻችን መካከልም ስማችን፣ የመኖሪያ አድራሻችን፣ ስልክ ቁጥራችን፣ የኢ-ሜይል አድራሻችንና ሌሎችን ግላዊ መረጃዎች ያካትታል። እነዚህን ግላዊ መረጃዎችን በኢንተርኔት ላይ መልቀቅ ወይም ማጋራት አደጋ ላይ ሊጥለን እንደሚችል መዘንጋት የለብንም። ሆኖም በኢንተርኔት ላይ የግል መረጃን ብናጋራ ሊያጋጥሙን ከሚችሉ አደጋዎች መካከልም የሚከተሉትን ይገኙበታል: የማንነት ስርቆት፤ የሳይበር ትንኮሳ፤ ከማያውቋቸው ሰዎች ፍቃደኛ ያልሆኑበት የመልዕክት ግንኙነቶች፤ በመረጃ አጥማጆች እጅ የመዉደቅና ሊጭበረበሩ ይችላሉ።

በእጅ ስልካችን ላይ ባሉ መተግበሪያዎች እንዳንሰለል ምን ማድረግ አለብን?

  በእጅ ስልካችን ላይ ባሉ መተግበሪያዎች እንዳንሰለል ምን ማድረግ አለብን? ====================== በየዕለቱ ህይወታችንን የሚያቀሉ ቴክኖሎጂዎች እየተፈበረኩ ሲሆን ሰዎች በነዚህ ውጤቶች ድካማቸውን አቅልለዋል፡፡ ይህ ጥቅም እንዳለ ሆኖ ግን እነዚህን መተግበሪያዎችን በመጠቀም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ መረጃዎቻችንን ይወስዳሉ፡፡ ለአብነትም መተግበሪያዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችንን ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች አሳልፎ መስጠጥ፣ የማስታወቂያ ድርጅቶች የገንዘብ ልውውጣችን ማወቅ፣ የመሸመት አቅማችንን፣ ዝንባሌያችንን እና ሌሎች ፍላጎቶቻችን ለማወቅ ይጠቅማሉ፡፡ ይህን ተከትሎ እንደ ቀልድ በእጅ ስልከችን ላይ ያወረድናቸው መተግበሪያዎች ከዋና አገልግሎቶቻቸው በተጨማሪ ያለ እኛ ፈቃድ ወይም ጉዳት አያመጡብንም በሚል አመለካከት መረጃዎቻችን እንዲወስዱ ፈቃድ ይወስዳሉ፡፡ ታዋቂው የበይነ መረብ ደህንነት ባለሙያው ዳረን ጉሲዮን ለኤኤአፍፒ እንዳሉት ሰዎች ስልካቸውን በሚገባ እንዲቆጣጠሩ አሳስበዋል፡፡ በተለይም ያለንበትን አካባቢ ወይም የአድራሻ መረጃን ለማንኛውም መተግበሪያ ፈቃድ ሊሰጥ አይገባም የሚሉት ባለሙያው ያለንበት አካባቢ ማለት ለማንኛውም ጥቃት መሰረት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የግድ አገልግሎት ለማግኘት አስፈላጊ ከሆነ ብቻ የአካባቢ ወይም ሎኬሽንን መፍቀድ እንደሚያስፈልግም አክለዋል፡፡ ያለንበት አካባቢ ማለት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ማስታወቂያ ለመልቀቅ፣ አንዳንዴ ከራሳችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያውቅብን ወደ ምንፈልገው ቦታ መሄድ ቢኖርብን፣ የምንጠቀመውን ኢንተርኔት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋይ እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን አሳልፎ ለመስጠት ዋነኛው ነውም ብለዋል፡፡ በብዙዎቻችን ስልክ ላይ ያሉት ሁሉም መተግበሪያዎች ቢችሉ አድራሻችንን መውሰድ ይፈልጋሉ የሚሉት ባለ...

የስፒር ፊሺንግ #spear_Phishing የሳይበር ጥቃት አይነት ምን ያክል ያዉቃሉ?

Image
የስፒር ፊሺንግ #spear_Phishing የሳይበር ጥቃት አይነት ምን ያክል ያዉቃሉ? የስፒር ፊሺንግ የሳይበር ጥቃት በተጠቂዉ አካል ላይ ቅድመ ዳሰሳ ተደርጎ የተሳካ ጥቃት ለመፈጸም የሚያስችል የሳይበር ጥቃት አይነት ነው፡፡ ይህም አጥቂዎች የተወነሰ ግለሰብን፣ ተቋምን ወይም ቡድንን ኢላማ ተደርገዉ የሚፈጽሙት የጥቃት አይነት ነዉ። የዚህ ጥቃት ሰለባ የሆነ አካል ሚስጥራዊ መረጃዎችን አሳልፈዉ እንዲሰጡ፣ አጥፊ ሶፍትዌሮችን እንዲያወርዱ #download እና ለአጭበርባሪዎች ገንዘብ እንዲልኩ ያደርጋቸዋል። ይህ ጥቃት በጥንቃቄ የሚፈጸም የፊሺንግ ጥቃት ሲሆን የሳይበር ወንጀለኞች ይህን አይነት ጥቃት ለማድረስ ኢላማ ባደረጉት አካል ላይ ሰፋ ያለ ጊዜ ወስደዉ ጥናቶችን በማድረግ ተጠቂዎችን ይለያሉ። በዚህ አይነት ጥቃት ኢላማ የሚደረገዉ አካል ላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታይ፣ የቅርብ ጓደኛ ወይም የስራ አጋር መስሎ የጥቃት ሙከራዎችን የሚያደርጉ ሲሆን አጥቂዎች ኢላማ ስላደረጉት አካል በቂ መረጃ ስለሚያገኙ በቀላሉ ጥቃት የማድረስ እድል ይፈጥርላቸዋል። እንዴት እንከላከለዉ? ይህ አይነት ጥቃት በስፋት በኢ-ሜይል መልዕክቶች አማካኝነት የሚፈጸም ሲሆን የተላኩልንን መልዕክቶች በደንብ ከመረመርነዉ ላኪዉ አካል ሃሰተኛ መሆኑን ለማወቅ አንቸገርም። በመሆኑም ይህን አይነት ጥቃት መደበኛ የፊሺንግ ጥቃት የምንከላከልበትን መንገዶችን በመከተል መከላከል የምንችል ሲሆን ከየትኛዉም አካል የሚላኩልንን የኢ-ሜይል መልእክቶች በጥንቃቄ በመመርመርና ሕጋዊ መሆን አለመሆናቸውን በመፈተሽ፣ የመልዕክት ላኪዉን አካል ትክክለኛነት ሳያረጋግጡ ምላሽ ባለመስጠት መከላከል እንችላለን።