የሰዎችን ስነልቦናና ባህሪይን በማጥናትና በመቆጣጠር ስለሚፈጸመዉ የሳይበር ጥቃት ምን ያክል ያዉቃሉ?
የሰዎችን ስነልቦናና ባህሪይን በማጥናትና በመቆጣጠር ስለሚፈጸመዉ የሳይበር ጥቃት ምን ያክል ያዉቃሉ?
የሰዎችን ስነ-ልቦናና ባህሪይን በማወቅና በመቆጣጠር የሚፈጸም የሳይበር ጥቃት አይነት ማህበራዊ ምህንድስና #social_engineering ጥቃት በመባል ይታወቃል። በጥቃቱ የግለሰብ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ወይም ሲስተሞችን ለመቆጣጠርና ጉዳት ለማድረስ የሰውን ልጆችን ስህተትና ድክመት እንደ መልካም እድል ይጠቀማል።
ይህ ጥቃት አይነትለወራት ወይም ለቀናት በኢ-ሜይል መልዕክት ወይም በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያና የተግባቦት መንገዶች በሚደረግ ክትትልና ግንኙነት ላይ በመመስረትና የተጠቂዉን ደካማጎን በመለየት ይፈጸማል።
የሰዎችን ስነልቦናና ባህሪይን በማጥናትና በመቆጣጠር የሚፈጸም ጥቃት #social_engineering ለማድረስ የሚከተሉት ደረጃዎች ይታለፋሉ፦
👉1. የጥቃት ኢላማ ስለተደረገዉ አካል መረጃ የመሰብሰብ ደረጃ፤
👉2. ግንኙነት በመመሥረት ወይም መስተጋብርን በመፍጠር እምነት የመገንባት ደረጃ
👉3. በድክመቶቹ ላይ ተመስርቶ ጥቃት መሰንዘሪያ ደረጃ
👉4. መረጃ ከወሰዱና አጥፊ ሶፍትዌር ካሰራጩ በኋላ ግንኙነቱን የማቋራጥ ደረጃ

Comments
Post a Comment