የስፒር ፊሺንግ #spear_Phishing የሳይበር ጥቃት አይነት ምን ያክል ያዉቃሉ?
የስፒር ፊሺንግ #spear_Phishing የሳይበር ጥቃት አይነት ምን ያክል ያዉቃሉ?
የስፒር ፊሺንግ የሳይበር ጥቃት በተጠቂዉ አካል ላይ ቅድመ ዳሰሳ ተደርጎ የተሳካ ጥቃት ለመፈጸም የሚያስችል የሳይበር ጥቃት አይነት ነው፡፡
ይህም አጥቂዎች የተወነሰ ግለሰብን፣ ተቋምን ወይም ቡድንን ኢላማ ተደርገዉ የሚፈጽሙት የጥቃት አይነት ነዉ። የዚህ ጥቃት ሰለባ የሆነ አካል ሚስጥራዊ መረጃዎችን አሳልፈዉ እንዲሰጡ፣ አጥፊ ሶፍትዌሮችን እንዲያወርዱ #download እና ለአጭበርባሪዎች ገንዘብ እንዲልኩ ያደርጋቸዋል።
በዚህ አይነት ጥቃት ኢላማ የሚደረገዉ አካል ላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታይ፣ የቅርብ ጓደኛ ወይም የስራ አጋር መስሎ የጥቃት ሙከራዎችን የሚያደርጉ ሲሆን አጥቂዎች ኢላማ ስላደረጉት አካል በቂ መረጃ ስለሚያገኙ በቀላሉ ጥቃት የማድረስ እድል ይፈጥርላቸዋል።
ይህ አይነት ጥቃት በስፋት በኢ-ሜይል መልዕክቶች አማካኝነት የሚፈጸም ሲሆን የተላኩልንን መልዕክቶች በደንብ ከመረመርነዉ ላኪዉ አካል ሃሰተኛ መሆኑን ለማወቅ አንቸገርም።
በመሆኑም ይህን አይነት ጥቃት መደበኛ የፊሺንግ ጥቃት የምንከላከልበትን መንገዶችን በመከተል መከላከል የምንችል ሲሆን ከየትኛዉም አካል የሚላኩልንን የኢ-ሜይል መልእክቶች በጥንቃቄ በመመርመርና ሕጋዊ መሆን አለመሆናቸውን በመፈተሽ፣ የመልዕክት ላኪዉን አካል ትክክለኛነት ሳያረጋግጡ ምላሽ ባለመስጠት መከላከል እንችላለን።
Comments
Post a Comment