አንድ የበቾ ገበሬ... የኛ ሃገር መሬት በትራክተር ሢታረሥ ምርቱን ይቀንሥብኛል የሚል ሃሣብ አወጋኝ።
አንድ የበቾ ገበሬ... የኛ ሃገር መሬት በትራክተር ሢታረሥ ምርቱን ይቀንሥብኛል የሚል ሃሣብ አወጋኝ።
~~~~~~
የ ደጀኔ አያት ጺምና ሚሥጥሩ!
[ቀመቀምኩኝ እንጂ አላጨውትም።😍]
የደጀኔ አያት ጺሙን ሁሌ በመቀሥ ይከመክማታል እንጂ ዝቅ ብሎ አይቆርጣትም።
"እንደ ድንች፣እንደ ጥበብ- ጥበቡ ያለው ከሥር ነው " ይላል በመሥታወት ውሥጥ አሻግሮ የጎሪጥ ደጀኔን እየተመለከተ።
¤
[በሬ ሆይ ሣሩን አይተህ ገደሉን ሣታይ...]
ደጀኔ የውርሥ እንጂ የእቅድ ገበሬ አይደለም። ይህንን ሃሣብ ግን ሁሌ ይከታተል ነበር።
እንደ አያቱ ጺም....
'እርሻዬ ከታች የተደበቀ ነገር ካለ በሚል እሣቤ ፣ የኔም እርሻ- አፈሩ ፣ማሣው ሚሥጥር ውሥጡ ይኖረዋል' በሚል አሥተውሎ....
የበሬዎቹ ጫንቃ እሥኪላጥ ፣ጅራፉ እሥኪበጣጠሥ፣ድምጹ እሥኪዘጋ፣እርፉ እሥኪሠበር ፣ሚሥቱ እሥክትደክም... እንዳበደ ገበሬ ማሣውን ቆፈረው፣ ጎደፈረው፣ አረሠው። በአዲሥ ማረሻው፣ ከ30cm በታች ሙሉውን መሬት ገለበጠው-(SPF)
sun protection factor አልገባውማ።
¤
ዘራበት!ተከለበት! እነ በቆሎ፣እነ ካሮት፣እነ ድንች ፣እነ ሥንዴ፣እነ ባቄላ፣እነ አኩሪ አተር፣እነ ሸንኮራ ተደሠቱ - አቆጠቆጡ። ሥሮቻቸው ድግሥ ወጡ፣ ቅጠሎቻቸው ተቻረሡ፣ግንዶቻቸው አሸበረቁ።ደሥ አላቸው።ቁመታቸው እኩል ነበር።
'ሥራችን ሠደደ፣አየራችን ተሥማማ፣ምግባችን በዛልን' አሉ።ተመቻቸው።
¤
[አሉም....]
'እኔ በቆሎ ሣድግ፣ሥመነደግ ብዙ ፍሬ ለጌታዬ አሥገኛለሁ። እንደ ድንች እራሤን ቀብሬ ብርሃን እጦት አያጠቃኝም ' አለ።
'እኔ ድንችሥ የአፈሩን አየር፣የምድሩን በረከት በገላዬ ሁሉ እየተመገብኩ ለጌታዬ ውጤትን አመጣለሁ፣እንደ በቆሎ ጸሃይ አይቀጠቅጠኝም ' አለ።
ሃ!ሃ!ሃ...' እኔ ባቄላሥ? ከብዙ ጥቅሜ የተነሣ ጌታዬ ይወደኛል፣የመጀመሪያ ምርጫው ነኝ።'
ሸንኮራ ' ያው ጌታችን እኮ ለምንሠጠው ጥቅም- አንዳንዶቻችንን ለፍሬአችን፣ እነ ድንችና ካሮትን ለሥሮቻቸው፣እንደኔ አይነቱን ለግንድ ነው የሚፈልገን።ሁላችንም እድሜአችን አጭር ነው። እነዛ የአፈር ውሥጥ ጓደኞቻችን ግን የት ጠፉ?! ይልቁን ቺርሥ!"
¤
[ ሥሻል ሣይኮሎጂ 010]
ከትንሽ ወቅት በኋላ ቁመታቸው ተለያየ፣ሥራቸው ለየቅል ሆነ የሚያመሣሥላቸው ጠፋ፣ድግሥ ቀረ።ነገር ግን በማፍሪያቸው ግዜ ያልተጠበቀው ተከሠተ።
የመሬት ትላትሎች ተቃወሙ ፣ አጉረመረሙ ።የፈንገሥ ዩኒየኖች ቅሬታ አሥገቡ። ማይክሮቦች ፣ተዋሢያን ወደ ጎረቤት ማሣ ተሠደዱ።ጸሃይ የማይችሉት እዛው ክው አሉ ። በሌሎች ተዋሢያን የተበሉም ነበሩ። ......
¤
[ምክር...]
አያት ይህንን ሁነት ተገነዘቡና "ልጄ!ጺሜን በየቀኑ ቀመቀምኩ እንጂ አላጨሁትም እኮ!?" አሉት።
ብዙ ጠልቆ ማረሥ የአፈሩን አወቃቀር ያበላሸዋል፣ ለእርሻ የሚጠቅሙን ነፍሣትን ይጎዳቸዋል ያበሣጫቸዋል ...እርሻም ከህዋሣት ጋር በመጠኑ ተሣሥቦና ተጠቃቅሞ መኖሩ ወደ ውጤት ይመራል እንጂ - ከራሥ ጥቅም አንጻር ብቻ ካለማወቅ አብዝቶ መሻት - ለጥቆም መፈጸም ተያይዞ ኪሣራ ያመጣል።
Social Interdependence Theory ...
This theory explains that when individuals understand their outcomes are linked (positively or negatively), their behavior changes.
Positive interdependence (mutual benefit) leads to cooperation, empathy, and trust.
Negative interdependence can cause competition or conflict.
¤
[አብዝቶ ጡዋራም ነጃሣ ነው። ]
¤
[አለባብሠው ቢያርሡም በአረም ይመለሡ ነው። ]
¤
ገበሬውን ከነበረው እሣቤ ከፍ የሚያደርግ፣ በሥፋትና በጥልቀት በአዲሥ የእርሻ ክህሎት የሚያደራጀው ጎበዝ ፣ማለፊያ ወጣት ያሥፈልጋል።
በርቱ!

Comments
Post a Comment