በስፋት እየተከሰቱ ያሉ ማጭበርበሮች በምን መልኩ ሊፈጸሙ ይችላሉ?

 በስፋት እየተከሰቱ ያሉ ማጭበርበሮች በምን መልኩ ሊፈጸሙ ይችላሉ?


ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሃገራችንም የሚከሰቱ የማጭበርበር ወንጀሎች ቁጥራቸዉ ክፍ እያለ መጥቷል። ከማጭበርበር

ጋር በተያያዘም ለሚመለከታቸዉ የህግ አስከባሪ አካላት በተደጋጋሚ ሪፖርቶች ይቀርባሉ። በመሆኑም ግለሰቦች የሚፈጸሙ ማጭበርበሮችን ለመከላከል በቅድሚያ በምን መልኩ ሊጭበረበሩ እንደሚችሉ ማወቅ ይገባል። በዚህ ጽሁፍም አጭበርባሪዎች በምን መልኩ ወደእኛ ቀርበዉ ሊያታልሉን የሚችሉበትን መንገድ እንጠቁማችሁ፡


👉#በፍቅር_ጓደኝነት_ስም

አጭበርባሪዎች የፍቅር ግንኙነትን ወይም ጓደኝነትን እንደ ወጥመድ ይጠቀማሉ። እነዚህ ግንኙነቱ እውነት እንዲመስል ጠንክረው የሚሰሩ ሲሆን የወጥመዳቸዉ ሰለባ የሆኑ አካላትን ከፍተኛ ገንዘብ ያጭበረብራሉ።  


👉#ትርፍ_ለማግኘት_ባለን_ፍላጎት 

ትርፍ ለማግኘት በምናደርጋቸዉ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ አጭበርባሪዎች እኛን ለማማለል በቀላሉ ብዙ ገንዘብ የምናገኝበት አማራጭ እንዳላቸዉ በማስመሰል ሁሉንም አይነት የማጭበርበር ዘዴ በመጠቀም ገንዘባችንን ይወስዳሉ። 


👉#የምርት_እና_አገልግሎት_አቅራቢ_በመምሰል

አጭበርባሪዎች ምርቶችን እና አገልግሎቶችን የሚገዙ ወይም የሚሸጡ በመምሰል ሰዎችን በማጥመድ ያጭበረብራሉ። 


👉#በማስፈራራትና_በዛቻ

አጭበርባሪዎች የእኛን ማንነት ወይም ገንዘብ ለማጭበርበር ማንኛውንም ታክቲክ የሚጠቀሙ ሲሆን ግላዊ መረጃዎቻችንን መጥለፍና ከመለጠፍ እስከ የግድያ ዛቻ በማስፈራራት ሊያጭበረብሩን ይችላሉ። 


👉#በስራ_ቅጥር_ስም 

ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኝ ሥራ እንደሚያስቀጥሩን በማግባባት ለቅጥሩ ቅድመ ክፍያ በመጠየቅ ገንዘባችንን አሳልፈን እንድንሰጣቸው በማድረግ ሊያጭበረብሩን ይችላሉ። 


👉#ድንገተኛ_ሽልማት

አጭበርባሪዎች ያልቆረጥነዉን ሎተሪ ወይም ያልተሳተፍንበትን ውድድር እንዳሸነፍንና ሽልማት እንዳገኘን በመንገር ሽልማቱን ለመዉሰድ ቅድመ ክፍያ ወይም ሚስጥራዊ መረጃ እንድንሰጣቸዉ በማግባባት ያጭበረብራሉ። 


👉#ያልሆኑትን_ሆኖ_በመቅረብ

አጭበርባሪዎች እምነት የሚጣልበት ተቋም፣ የቅርብ ወዳጅ ወይም ቤተሰብ መስሎ በመቅረብ ገንዘብ የማጭበርበር ወይም መረጃ የመመንተፍ ድርጊት ይፈጽማሉ።




Comments

Popular posts from this blog

የስፒር ፊሺንግ #spear_Phishing የሳይበር ጥቃት አይነት ምን ያክል ያዉቃሉ?

የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት እና የአደጋ ስጋት መኖሩን ከተረዳን እንደ ተቋም ሊወሰዱ የሚገቡ ቀዳሚ እርምጃዎች ምንድን ናቸው?